መለያችን ደራሽነታችን!!

የተሽከርካሪ ብዛት
በስራው ላይ ያለን ልምድ
የተሰጡ አገልግሎቶች
ደንበኞቻችን
ዕለት ደራሽ የእርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ እና የጭነት ትራንስፖርት ታሪክ ውስጥ የማይጠፋ ዘላቂ አሻራ ያሳረፈ፣ በአስተማማኝነቱና በፈጣን ደራሽነቱ የሚታወቅ አንጋፋ የመንግሥት የልማት ድርጅት ሲሆን፤ ስትራቴጂካዊ ተልዕኮውንም በሁለት አበይት ምሶሶዎች ላይ መስርቶ ይንቀሳቀሳል። በአንድ በኩል፣ በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ምክንያቶች ለሚከሰቱ አደጋዎች ፈጣንና ቀልጣፋ የድንገተኛ እርዳታ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሕብረተሰቡ በማድረስ የዜጎችን ሕይወት የመታደግ አጣዳፊ አገራዊ ኃላፊነቱን በቁርጠኝነት የሚወጣ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ፣ የአገሪቱን የንግድ ፍሰትና የኢኮኖሚ ቀጣይነት ለማረጋገጥ የጭነት ትራንስፖርት አቅሙን በማሳደግና አስተማማኝ የሎጂስቲክስ ሰንሰለት በመዘርጋት ለንግዱ ማኅበረሰብና ለሀገር ዕድገት የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ከተቀመጡት ዋና ዋና ዓላማዎች በተጨማሪ ድርጅቱ ለረጅም ዓመታት ባካበተው ሰፊ ልምድ ለበርካታ የመንግሥትና መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ደረጃውን የጠበቀ የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን፣ ለዚህ ስኬቱ ደግሞ አስተማማኝ ሰላም፣ የተሟላ የተሽከርካሪዎች ስምሪት ዝግጁነት፣ የሰለጠነ የሰው ኃይል እና ዘመናዊ አሰራርን በአግባቡ መጠቀም መቻሉ ቁልፍ ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሮለታል።

ዋና ስራ አስፈጻሚ
የድርጅታችን ራዕይ፣ ተልዕኮ እና እሴቶች ለዘላቂ እድገትና ለላቀ አገልግሎት መሠረት ናቸው።

"በ2020 በኢትዮጵያ ተመራጭና ተወዳዳሪ የዕርዳታና የንግድ ጭነት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ሆኖ መገኘት"

የዕርዳታ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት፤ ማንኛውንም የንግድና የልማት ጭነት አገልግሎት መስጠት፤ የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት መስጠት፣ ዓላማዎቹን ከግብ ለማድረስ የሚያግዙ ሌሎች ተዛማጅ የገቢ ማስገኛ ሥራዎችን ማከናወን።

ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንሰጣለን።
የድርጅቱን መልካም ስምና ዝናን ጠብቀን እናቆያለን።
ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን።
ሀብትን በቁጠባ በመጠቀም ለወጪ ቅነሳ ልዩ ትኩረት እንሰጣለን።
የውጤታማነታችን መለኪያ የደንበኞቻችን እርካታ ነው።
የሠራተኞቻችንን ጤንነት ከበሽታ መከላከል የሥራችን አካል ነው።
ለሕሊናችን እና ለማህበረሰባችን ታምነን እንሠራለን።
ድርጅታችን በከፍተኛ ጥራት፣ በፍጥነት እና በአስተማማኝነት የተለያዩ የትራንስፖርትና የጥገና አገልግሎቶችን ይሰጣል።

የዕርዳታ እህልና ቁሳቁስ ከአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ማዕከላዊ መጋዝኖች ወደ ተለያዩ የአገራችን ክፍሎች በፍጥነት እና በደህንነት የማጓጓዝ አገልግሎት እንሰጣለን።

የማንኛውንም የንግድ ጭነቶችን በአገር ውስጥ እና ከወደብ ወደ አገር ውስጥ በዘመናዊ የሎጂስቲክስ ስርዓት በመጠቀም በአስተማማኝ ሁኔታ እናጓጉዛለን።

ለከባድ፣ ለመካከለኛ እና ለቀላል ተሸከርካሪዎች የሜካኒካል፣ የኤሌክትሪክ እና የቦዲ ጥገና አገልግሎት በብቁ ባለሙያዎች እንሰጣለን።

የአንዱ የመጫን አቅም: 400 ኩንታል
ብዛት: 70

የአንዱ የመጫን አቅም: 510 ኩንታል
ብዛት: 15

የአንዱ የመጫን አቅም: 400 ኩንታል
ብዛት: 100
የቅርብ ጊዜ ዜናዎቻችንን፣ የድርጅት ዝማኔዎችን፣ የሥራ ስኬቶችን እና አስፈላጊ ማስታወቂያዎችን ይመልከቱ።
ዕለት ደራሽ የሙያ ደረጃዎችን ይጠብቃል እንዲሁም ከአገር አቀፍ እና ከአለም አቀፍ የትራንስፖርት፣ የሎጂስቲክስ፣ የደህንነት እና የጥራት አስተዳደር መስፈርቶች ጋር ይጣጣማል።
የድርጅቱ ዋና መ/ቤት በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ሲሆን፣ በኮምቦልቻ፣ ያቤሎ እና አዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችም አሉ።

አዳማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

ጅቡቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

ኮምቦልቻ ማስተባበሪያ ጣቢያ

ድሬዳዋ ማስተባበሪያ ጣቢያ

ያቤሎ ማስተባበሪያ ጣቢያ

ሚሌ ማስተባበሪያ ጣቢያ
በሕዝብ እና በግል ዘርፍ አጋሮች የምንታመን ነን - ከታች ያሉት አርማዎች ተወካይ ናቸው።
በሕዝብ እና በግል ዘርፍ አጋሮች የምንታመን ነን - ከታች ያሉት አርማዎች ተወካይ ናቸው።